የረድዔት አገልግሎት መተዳደሪያ ደንብ

ኣንቀጽ 1: ራዕይ

የረድዔት አገልግሎት ራዕይ በ2ኛ ቆሮንጦስ ምዕራፍ 9 ቁ12 ላይ “ለቅዱሳን የሚጎድላቸውን በሙሉ የሚሰጥ ብቻ አይደለምና ፥ ነገር ግን ደግሞ በብዙ ምስጋና ለእግዚእብሔር ይበዛል፣” የሚለዉን ጥቅስ መነሻ በማድረግ ወገኖቻችንን በመርዳት ለእግዚእብሔር ምስጋና እንዲበዛ ለማድረግ ነው።

ኣንቀጽ 2: ዓላማው

እርስ በርስ ለመተዋወቅና ለመተጋገዝ ብሎም ክርስቲያናዊ ቤተሰብነትን ለማዳበር እንዲረዳ ሃዘን በደረሰ ጊዜ ሃዘኑ ከደረሰባቸው ቤተሰቦች ጋር አብሮ በመቆም ለማጽናናትና በሃዘኑ ምክንያት በዋናነት የሚደርሰውን ወጪ በገንዘብ ለማገዝ የተቋቋመ መረዳጃ ማሕበር ነው።

ኣንቀጽ 3: ስያሜው

የዚህ መረዳጃ ማሕበር መጠሪያ ስም በብሪታኒያ የኢትዮጵያ ወንጌላዊ ክርስቲያኖች ኅብረት ቤተ ክርስቲያን የረድዔት ኣገልግሎት ተብሎ ይጠራል።

ኣንቀጽ 4: የኣገልግሎቱ ኣወቃቀር

  1. ይህ አገልግሎት ተጠሪነቱ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የኣባላት እንክብካቤ ኣገልግሎት ዘርፍ ሆኖ የራሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይኖረዋል።

  1. ለዚህ አገልግሎት ሸክምና ፍላጎት ያላቸውን አባላት በአመራሩ እንዲካተቱ ያበረታታል።

ኣንቀጽ 5: የሥር አስፈዳሚ ኮሚቴ

  1. ለአገልግሎቱ ጠቃሚ የሆኑ ሃሳቦችንና ማሻሻያዎችን አጥንቶ የማጠናከሪያና የውሳኔ ሃሳብ ለኣባላቱ ጠቅላላ ጉባዔ በማቅረብ ያስወስናል።

  1. የውሳኔ ሃሳቦች እነደ አስፈላጊነቱ ለጠቅላላ ጉባኤ በማቅረብ ዉሳኔ ያሰጣል።

  1. በሐዘን ጊዜ አባላት የሚረዱበትን መንገድ ያዘጋጃል።

  1. ለአገልግሎቱ ኣስፈላጊ ዕቃዎች እንዲገዙ ይወስናል።

  1. አገልግሎቱን የሚመሩ አምስት የሥራ አስፈጻሚ አባላት ሲኖሩት እነርሱም ሰብሳቢ፣ ሂሳብ ሹም፣ ጸሐፊና ሁለት አባላት ናቸው።

ኣንቀጽ 6: የሥራ እስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ጸሐፊና የሂሳብ ሹም የሥራ ድርሻ፣

ሀ/ የሰብሳቢው ተግባርና ሀላፊነት

  1. መተዳደሪያ ደንቡን ያስፈጽማል።

  1. ስብሰባዎችን ይመራል።

  1. የገንዘብ ወጪ ሲያስፈልግ ከሂሳብ ሹሙ ወይም ቼክ እንዲፈረም/ አንድትፈርም ሥልጣን ከተሰጥው/ጣት ጋር በመሆን ቼክ ይፈርማል። በጥሬ ገንዘብ እና በሌላ መንገድ የሚካሄዱ ውጪዎችንም ያደድቃል።

  1. በድምጽ ኣሰጣጥ ወቅት እኩል ሲሆን እርሱ የደገፈው የጸና ይሆናል።

  1. የውሳኔ ሃሳቦችን ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በማቅረብ ያስወስናል።

  1. ወረሃዊ ሪፖርቶች ለመእመን እንክብካቤ አገልግሎት ዘርፍ በውቅቱ መድረሱን ያረጋግጣል።

  1. ለአገልግሎቱ ኣስፈላጊ ዕቃዎች እንዲገዙ በሥራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ያስወስናል፣ ከተወሰነ በኋላም ግዥዉ እንዲፈጸም ትእዛዝ ይሰጣል።

  1. ሃዘን ከደረሰባቸው ቤተሰብ ጋር በመመካከር የቀብሩን ስነስርኣት ያስፈጽማል።

የመቀበሪያ ሳጥን፣ መኪና፣ አበባና የመቀበሪያ ቦታ በማዘጋጀት ረገድ እገዛ ያስደርጋል።

  1. ከቀብር በኋላ የሟች ቤተሰቦች በመረጡት ቦታ ምግብ እና መጠጥ እስተባብሮ ያዘጋጃል ፣ ያስተናግዳል።

ለ/ የጸሐፊው ተግባርና ሀላፊነት

  1. ቃለ ጉባኤዎችን ጽፎ ይይዛል ከሰብሳቢውም ጋር በመነጋገር የስብሰባ አጀንዳዎችን ያዘጋጃል።

  1. የረድዔት አባላትን ስም ዝርዝር መዝግቦ ይይዛል፤ የአባልነት ቅጽ መሞላቱንም ያረጋግጣል።

  1. ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎችን ሰብሳቢው በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ያከናውናል።

ሐ/ የሂሳብ ሹሙ ተግባርና ኅላፊነት

  1. የማህበሩ አባላት ወርሃዊ መዋጮ መክፈላቸዉን ይቆጣጠራል መዝግብም ይይዛል። በወቅቱ መዋጮአቸዉን ላልከፈሉ አባላት ቀሪውን እንዲከፍሉ ማሳስቢ ይልካል።

  1. ቼክ ከሚፈርሙት መካከል አንዱ ይሆናል።

  1. ለረዥም ጊዜ ባልከፈሉ አባላት ላይ ሊወሰድ የሚገባው ዕርመጃ መወሰድ እንዲኖርበት ለሥራ አስፈዳሚ ኮሚቴው በጊዜው ያሳውቃል።

  1. አገልግሎቱ ያለበትን የሂሳብ ሁኔታ የሚገልድ ወቅታዊ የሂሳብ ሪፖርት ለሥራ አስፈዳሚው ያቀርባል፤ እንደአስፈላጊነቱም እርመጃ መወሰዱንም ያረጋግጣል።

  1. ሐዘን ለደረስበት ሊከፈል የሚገባው £6,000.00 ቼክ መዘጋጀቱንና ለተገቢውም ሐዘነተኛ ቼኩ መድረሱን ያረጋግጣል።

ኣንቀጽ 7:የአባላት እንክብካቤ ዘርፍ ኃላፊነት

  1. የመተዳደሪያ ደንቡ በተግባር እንዲተረጎም ያደርጋል። መተረጎሙንም የሚገልድ ወርሀዊ ሪፖርት ከሥራ አስፈዳሚው ይቀበላል። አለመተርጎሙንም ሲያረጋግጥ የዕርምት ዕርመጃ እንዲወሰድ ያዛል፤ ዕርምጃው መወሰዱንም ያረጋግጣል።

  1. ለኣገልግሎቱ ጠቃሚ የሆኑ ሃሳቦችንና ማሻሻያዎችን አጥንቶ በተግባር እንዲውሉም ለሥር አስፈዳሚ ኮሚቴ ትእዛዝ ይሰጣል።

ኣንቀጽ 8: የረድዔት አባላት

  1. በብሪታንያ የኢትዮጵያ ወንጌላዊ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተክርቲያን አባል የሆነ ወይም የሆነችና ለረድዔት አገልግሎት የሚዋጣውን ወርሃዊ መዋጮ በትክክልና በጊዜው ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ/ች ሁሉ ኣባል መሆን ይችላል/ ትችላለች።

  1. ኣባላት የራሳቸውንና የመላ ቤተሰቦቸውን ስም ዝርዝር በኣባልነት መመዝገቢያ ቅጽ ላይ መሙላት ይኖርባቸዋል። በዚህ እገልግሎት ቤተሰብ ማለት፦

  • ባል ፣ ሚስትና ልጆች ናቸው

  • ልጆች ማለት እድሜያቸው ከ 0 እስከ 18 አመት ያሉትን ማለት ነው፡፡

  1. ከ 18 አመት በላይ ያሉ ልጆች በራሳችቸው ፎርም ሞልተው አባል መሆን ይችላሉ፡፡

  1. የቤተክርስቲያኒቱ አባልነት ወሳኝ በመሆኑ፤ ሐገር ሲቅይርም (ስትቀይርም) ሆነ በተክርስቲያኒቱን በተለያየ ሁኔታ ቢለቅ (ብትለቅ) አባልነቱ ይቀራል፤ የተከፈለውም መዋጮ አይመለስም።

ኣንቀጽ 9: የረድዔት አባላት መብት እና ግዴታ

መብት

አንድ የረድኤት ኣባል ሃዘን ሲደርስበት፦

  1. የገንዘብ እርዳታው እላይ በአንቀድ 6ሐ 5 የተጠቀሰው £6,000.00 ይከፈለዋል፣

  1. የቀብር ስነስርአቱን ለማስፈጸም እገዛ ይደረግለታል፤

  1. የምክር እና የመሳሰሉትን ዕርዳታ ያገኛል።

ግዴታ

  1. የተመደበውን ወርሃዊ መዋጮ በታማኝነት መክፈል፤ መዋጮው በየወሩ ወይም በየዓመቱ መጀመሪያ (May) በታች በተጥቀሰው በቀጥታ ገቢ ማድረግ፤

  1. የአገልግሎቱ አስተባባሪዎች ርዳታ ሲጠይቁ ለጥሪው መተባበር፣

  1. የወርሀዊው መዋጮው መጠን፦

  • አንድ ቤተሰብ = 6 ፓውንድ

  • ሁለት ቤተሰብ = 8 ፓውንድ

  • ሶስት ቤተሰብ = 10 ፓውንድ

  • አራትና ከዚያ በላይ ቤተስብ ያላችው =12 ፓውንድ

  1. ኣንድ አባል በገባው ስምምነት መሰረት የሶስት ተከታታይ መዋጮዉን ባይከፍል የዚህ ማሕበር አገልግሎት ተጠቃሚ አይሆንም።

  1. አንድ አባል መዋጮዉን ሲከፍል ቆይቶ ወደ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ቢሄድ ወይም ሀገር ቢቀይር ከአባልነቱ ይስረዛል፡፡ የከፈለውም መዋጮ አይመለስለትም።

  1. የቤተሰብ አባል ሲጨምር ወይም ሲቀንስ ለአገለገሎቱ የማሳውቅ ግደታ አለበት፡፡

  1. የልጆች እድሜ 18 ሲሞላ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡ ልጆቹንም እንደ አዲስ አባል ራሳቸውን ችለው እነዲመዘገቡ ማስደረግ ይቻላል፤

  1. ከMAY 2022 ጀምሮ የቤተክርስቲያን አባል የሆነና የረድኤት አባል መሆን የሚፈልግ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መመዘገቢያ መክፈል ይጠበቅበታል።

  • ቤተሰብ 1= 72 ፓውንድ

  • ቤተሰብ 2 = 96 ፓውንድ

  • ቤተሰብ 3= 120 ፓውንድ

  • ቤተሰብ 4= 144 ፓውንድ

በተጨማሪም የአባልነት ጥያቄው ተቀባይነት ማግኘቱ ከተረጋግጠበት ጊዜ ጀምሮ ወርሃዊ መዋጮውን መክፈል ይኖረበታል።

ኣንቀጽ 10 :

ለረድኤት ኣገልግሎት መነሻ ገንዘብ የቤተክርስቲያን መሪዎች በፈቃደኝነት የሰጡት £6,000.00 ነው።

ኣንቀጽ 11:

ይህ መተዳደሪያ ደንብ እንደ ኣስፈላጊነቱ በአገልግሎቱ መሪዎች እየተጠና ለጠቅላላው ጉባኤ ቀርቦ ሊሻሻል ይችላል።

Bank details

Radiate Social Club

Lloyds Bank plc

Sort code = 30-99-50

Account no = 70544468